Home Page - ethiotoday

freedom of press and democracy for ethiopia
Go to content

Main menu:


        

             

 
 
 

መንግስት የሌው እዚ ብቻነው.....ይለያል ዘንድሮ የ ወያኔ ኑሮ .....አንመካም በጉልበታችን እግዚያቢሔር ነው ....ሌባ ሌባ ወያኔ ሌባ....ከአባይ በፌት ደማችን ይገደብ ...ከአባይ በፌት እምባችን ይገደብ ...እኛን ከምትደበድቡ አይ ሲ ስን ደብደቡ !! የመረው የተጨቆነው እስከ ዛሬ በዝምታ ላይ የነበረው ወገኔ ወደ መጨረሻው ምእራፍ ላይ እየደረሰ ነው !! ትግላችን እስከ ቀራንዬ ድረስ ነው !!
  

የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያቀረቡት አስቸኳይ ጥሪ
April 22, 2015 | Filed underEditorial & News,አማርኛ | Posted by admin

የተከበራችሁ ወገኖቼ፤ ከሰላሳ በላይ የሆኑ ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ከትናንት ወዲያ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓም ደርሶን ኢትዮጵያዊያን በያለንበት በመሪር ሀዘን ውስጥ ነን። ዛሬ “እግዜር ያጥናህ” ወይም “እግዜር ያጥናሽ” የሚባል ሰው የለም። ሁላችንም ሀዘንተኞች ነን። ካጣናቸው ቁጥራቸው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ወገኖቻችን አሁንም በአራዶች መዳፍ ውስጥ መሆናቸው ሀዘናችን እጅግ የበረታ ያደረገዋል። ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ ሆኖም በሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን ዛሬም ሊቢያ ውስጥ ናቸው። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሁንም ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ናቸው። ሌሎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ደግሞ በየመን ከሰማይም ከምድርም በቦንብና በጥይት እየተማገዱ ነው።

ለምንድነው ኢትዮጵያዊያን እንዲህ እሳት ውስጥ ለመማገድ የምንደፍረው? መልሱ ግልጽ ነው። አገር ውስጥ ተስፋ የለም፤ ወያኔዎች ተስፋችንን አጨለሙት። ከሳዉዲ በመከራ የተመለሱ ወንድሞቻችን ናቸው በሊቢያ በኩል ለመሰደድ ሲሞክሩ በአይ ሲስ ተይዘው የታረዱት። ወያኔዎች አገራችንና ክብራችን ዘረፉን። ወያኔዎች ስብዕናችንን ገፈፉን።
የዘመኑ ጥቂት የህወሓት ቱጃሮች ፎቆችን እየገነቡ በነሱ መጥገብ እኛ እንድናገሳላቸው ይፈልጋሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ መራቡ፣ መታረዙ፣ መደህየቱ እውነት ነው፤ ሆኖም ግን “ተራብኩ”፣ “ታረዝኩ”፣ “ደኸየሁ” ብሎ መናገር አይችልም። እውነት መናገር ያስቀጣል፣ ያስወነጅላል። በፍርደ ገምድል ችሎት እውነት መናገር “ሽብርተኛ” ያስብላል። እስር ቤቶችን የተሞሉት ለእውነት፣ ለፍትህ፣ ለነፃናትና ለእኩልነት በቆሙ ሰዎች አይደለምን?
በአይ ሲስ ያሳረደን ማነው? መልሱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ ነው። ያዋረደን፣ በአይ ሲስ ቢላዋ ያሳረደን ህወሓት ነው። እንደ አገርና እንደ ሕዝብ የደረሰብን ውርደት የትም ብንሄድ የምናመልጠው አልሆነም። በአገር ውስጥ የደረሰብንን ውርደት ለማምለጥ ስንሰደድ ውርደት ተከትሎን ይመጣል።
ወገኖቼ፤ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ የተሻለች አገር ሊኖረን አይችልም። ዛሬ የመሸሻ ጊዜ አይደለም። አገራችንን ከወያኔ ነጥቀን፤ በአገራችን ኮርተን በሰላም መኖር እንሻለን። ይህ መብታችን ነው። አገራችን የኛ ነች። አገራችን የጥቂት ወያኔዎች መፈንጫ አይደለችም።
  ወገኔ፤ ዛሬ ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም በአርበኖች ግንቦት 7 ስም የማደርግልህ ጥሪ አድምጠኝ። በሀይማኖት፣ በብሔር፣ በጾታ ልዩነት ሳታደርግ ዛሬ በአንድነት እንደተሳህ አንድነትህን እንደጠበቅህ ቀጥል። አንድነትህን ለመሸርሸር ወያኔ የማይፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም፤ ለወያኔ ዱለታ ጆሮህን አትስጥ። የወያኔ አገዛዝ እንዲያበቃ በአንድነት ተነስ። ዛሬ የጀመርከው ትግል እዳር ሳይደርስ እረፍት የለንም።
   ርበኞች ግንቦት 7፣ ከትግራይ፣ ከኦሮሚያ፣ ከአፋር፣ ከኦጋዴን፣ ከጋምቤላ፣ ከቤሻንጉል ድርጅቶች ጋር በመጣመር የአገር አድን ኃይል የመገንባት ሥራውን እያጠናቀቀ ነው። እኛ ልጆችህ በብሔርም ሆነ በሀይማኖት ሳንከፋፈል፤ ከትግራይ እስከ ኦጋዴን፤ ከአፋር እስከ ጋምቤላ ሁሉንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ባካተተ ስብስብ ውስጥ አብረን ህወሓትን እየታገልን ነው። ይህ ትግል ግን የአንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ነው። የትግሉም የአገሪቷም ባለቤት አንተ ነህ። ስለሆነም ተነስ! “እንቢኝ” በል። ዘርፈ ብዙ የትግል ስልቶችን በመጠቀም ወያኔን አዳክም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! በትግልህ ፍሬ የአገርህ ባለቤት ሁን።
 መከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ሆይ!እናንተ የሕዝብ አካላት ናችሁ። የደረሰብንን ብሔራዊ ውርደት እያያችሁ፤ እሮሮዓችን እየሰማችሁ በሕዝብ ላይ መተኮስ በራሳችሁ ጭንቅላት ላይ መተኮስ ማለት መሆኑን ለደቂቃ እንኳን አትዘንጉ። ይልቁኑ ዛሬውኑ ነፃነትና ፍትህ ከጠማው ወገናችሁ ጎን ቁሙ።
የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ የወጣትነት የፈጠራ ችሎቻችሁ መፈተኛው አሁን ነው። ለእያንዳንዱ ጥቃቅን ጉዳይ መመሪያ እስኪሰጣችሁ አትጠብቁ። እያሰላችሁ፣ እያጠናችሁ፣ እያደባችሁ፣ ወያኔን ታገሉ።
የታፈረች፣ የተከበረችና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን።
   ብርሀኑ ነጋ
   የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር
   ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም

በአዲስ አበባ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፣ ሰልፈኛው በሊቢያ የኢትዮጵያውያንን መገደልና መንግስት ያሳየውን ቸልተኛነት በመቃወም ላይ ነው

April 21, 2015

UPDATE:
**** ሰበር ዜና፣ ሰልፈኛው የኢቲቪ/ ኢብኮ ጋዜጠኞችን ደበደበ ****

(ነገረ-ኢትዮጵያ) ከደቂቃዎች በፊት የኢቲቪ/ ኢብኮ ጋዜጠኞች በለቀስተኞች መደብደባቸው ተሰምቷል፡፡ የኢትቪ /ኢብኮ ጋዜጠኞች ለቅሶ ቤት ውስጥ ቀረጻ አድርገው ሲመለሱ ‹‹ሌቦች እናንተ ልታስተላልፉት አይደለም፡፡ ስለ እኛ ምን አገባችሁ?›› ተብለው እንደተደበደቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡
—————————
በሊብያ አሸባሪዎች በኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸሙትን አሰቃቂ ግድያ ለማውገዝና መንግስት ነኝ ባዩ ወያኔ ያሳየውን ቸልተኛነት ለመቃወም በአዲስ አበባ ህዝቡ ነቅሎ አደባባይ ወጥቷል።
ይሁንና ፖሊስ እንደተለመደው ሰልፉን ለመበተን ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፣ ነገረ-ኢትዮጵያ እንደዘገበው ከሆን ፖሊስ ሰልፈኛውን በዱላ መደብደብ ጀምሯል።
ሰልፉ ከፖሊሶቹ ቁጥጥር በላይ ሆኗል፣ በርካታ ህዝብ እየጮኸ እና እያለቀሰ ሰልፈኛውን መቀላቀሉን ቀጥሏል።
ሰልፈኞቹ ከሚያሰሙት መፈክሮች መካከል፣
‹ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት የለም!››
‹‹መንግስት የሌለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው!››
‹‹የወንድሞቻችን ደም በከንቱ ፈሶ አይቀርም!››
‹‹የወንድሞቻችን ደም ውሃ አይደለም!››
ሰልፈኛው በተለይ ወጣቱ በቁጭት ለሟቾቹ ትኩረት ያልሰጠው መንግስት ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰማ ነው!
         ‹‹ሌባ! ሌባ!ሌባ! ሌባ!ሌባ! ሌባ!››
ሰልፉ ቀጥሏል፣ ፖሊስ ሰዎች ሰልፈኛውን እንዳይቀላቀሉ ጥረት እያደረገ ነው።
ለቀጥታ ዘገባ የፌስቡክ ገጻችንን ይከታተሉ

Statement of Patriotic Ginbot 7 on Fellow Ethiopians who were Victims of barbarians.
April 20, 2015
Ginbot7                                                                         

            It is with deep distress that the people of Ethiopia have heard the barbaric killing of twenty eight fellow Ethiopians in Libya on April 19, 2015 by the barbaric and medieval cowards of ISIS. This group, who belong to the darkest of dark ages, and takes pleasure of its barbarism, has killed desperate, defenseless Ethiopian migrants who have no other objective other than seeking a better life outside of their country. By so doing, the barbaric and criminal beasts have demonstrated beyond the shadow of a doubt that they have a serious quarrel with humanity itself, not to mention the fact that they dont even know what prophet Mohammad, in whose name they kill, has said about Ethiopia and Ethiopians in the wholly book and the story of the Fist Hegira.
Patriotic Ginbot 7 for Unity and Democracy Condemns this heinous crime on our fellow citizens and calls on all Ethiopians to condemn it in no uncertain and clear terms and put up a united fight against this barbaric group in all ways and means we can.
We also take this opportunity to reiterate the fact that the barbaric terrorism perpetrated by this group which calls itself ISIS, has nothing to do with the religion of Islam as what it does is against the teachings of Islamic. Our country Ethiopia is holy to both Moslems and Christians. Moslems and Christians in in Ethiopia live and have lived as a family harmonisly , exemplary tolerance and respect of one anothers religions. As Ethiopians, we will keep priding ourselves of this exemplary unity between Moslems and Christians and consider it as pivotal feature for our survival as a country in bad and good times for over millennia.
The tragedy that has befallen on our fellow country and people over the last week has not been only the murder of our fellow Ethiopians in Libya. In South Africa fellow Ethiopians were also murdered in cold blood and burned with fire alive. During the same week we have also heard the drowning of a ship in the Mediterranean Sea that we believe has carried large number of Ethiopians who perished along with 700 other people. In Yemen thousands of Ethiopians are living in the middle of the hell of war.
Ethiopians who flee injustice and economic hardship in their country are facing humiliation, death and hopelessness in a way that we have rarely seen in our history. There is no question that the source of all these hardship is the corrupt dictatorship of the TPLF that is ruling Ethiopia with iron fist and with callous disregard for the welfare of Ethiopians. We, as an organization of democracy and justice, believe that the removal of this regime from power is the only way to reverse this tragedy that we are subjected to live in. For Ethiopians, there is no place better than Ethiopia and we are determined to make it one.
Patriotic Ginbot 7 calls on Ethiopians to once and for all end this tragedy by fully engaging in the struggle everywhere, in places where we live and work , contribute towards an organized resistance to the TPLF brutal rule. We call on all Ethiopians from all walks of life , including Ethiopians of every religion and ethnic group to come together, join hands and struggle in unison to remove this regime. We can never forget that the TPLF is the source of this unending tragic life of our people.
Eternal peace for those who lost their lives by barbarians
facebook

twitter
rss
emailወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው
April 2, 2015 | Filed underG7 Editorial,Slider Post | Posted by admi
ለገዛ ራሱ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያ ቅን የሚመኝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ህወሓትን ለማስወገድ ተግባራዊ ትግል ውስጥ መሳተፍ የሚኖርበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በዚህ ወሳኝ ወቅት ከዳር ሆኖ መታዘብ ዘረኛውን፣ አምባገነኑን፣ ፋሽስቱን ህወሓት እንደመደገፍ ይቆጠራል።
ዛሬ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህሊናውና አቅሙ በሚፈቅድለት የትግል ዘርፍ የመሰማራት ሰፊ እድል ተፈጥሮለታል። በዚህም መሠረት የህወሓትን አፈና በጠነከረ ክንድ ለመመከት የቆረጡ ኢትዮጵያዊያን ወደ በረሃዎችና ተራራዎች አቅንተዋል። ብዙዎች በመንገዱ ላይ ያሉ ጋሬጣዎችን ተቋቁመው እየተቀላቀሏቸው ነው። በደል የመረራቸው ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በቡድን ለነፃነታቸው ዘብ ቆመው በህወሓትና አገልጋዮቹ ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ይህ የሚበረታታ እና ተቀናጅቶ ሊጠናከር የሚገባው ጉዳይ ነው።
አሁን ያለንበት ጊዜ ልዩ የትግል ወቅት ነው። ትናንት በከተሞች ይካሄድ የነበረው ፀረ ወያኔ ትግል ዓይነተኛ መታወቂያው ሕዝባዊ ተቃውሞ ነበር። ዛሬ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል። በተለይ በአገዛዙ ፈቃድ የሚደረጉ ተቃውሞዎች ፋይዳ ቢስ ሆነዋል። በአገዛዙ ፈቃድ በሚደረጉ ተቃውሞዎች ለውጥ እንደማይመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ ተረድቷል። ስለሆነም ትግሉ ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት አድጓል።
ዛሬ ከዚህ በፊት ያልተሞከሩ የትግል ስልቶች ተግባራዊ እየሆኑ ነው። በዚህ ረገድ የሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የተቀናጁ ርምጃዎች በአርዓያነት የሚጠቀሱና የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ የሚሹ ናቸው። እነዚህ የሕዝባዊ እምቢተኝነት ተግባራት የእምነት አጥር ሳይለያየን ፍትህ የተጠማን ዜጎች ሁሉ ልንተገብራቸው የሚገቡ ናቸው።
ለምሳሌ፣ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በተወሰኑ ቀናት መዝጋት በተቀናጀ ሁኔታ ከተደረገ ከፍተኛ ውጤት ሊያመጣ የሚችል፤ በሙስሊም ወገኖቻችን ግንባር ቀደም መሪነትና አስተባባሪነት ተሞክሮ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል መሆኑ የታየ አንድ የትግል ስልት ነው።
በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ በመደረግ ላይ ያለው ሣንቲሞችን የመሰብሰብ ዘመቻም ሌላ ከዚህ በፊት ያልተሞከረ፤ በተጨማሪ እርምጃዎች ከታገዘ ህወሓት መራሹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን ገንዘብ መቆጣጠር የማይችልበት ደረጃ ላይ ሊያደርስ የሚችል ጉልበት ያለው ስልት ነው። ውሳኔው ሣንቲሞችን ብቻ ሳይሆን የወረቀት ኖቶችንም ሲያካትት በዝውውር ላይ የሚኖረውን ገንዘብ ብዛት የሚቆጣጠረው ህወሓት ሳይሆን በደል ያንገሸገሸው ሕዝብ ይሆናል። በባንኮች ያለ ተቀማጭ ገንዘብ በማውጣትም የህወሓት የፋይናንስ ተቋማትን ማሽመድመድ ሌላ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ስልት ነው። በእነዚህ እርምጃዎች የተለማመደ ሕዝብም ወደ ግዢ እቀባ፤ ለተወሰኑ ቀናት ከቤት አለመውጣት ብሎም “ግብር አልከፍልም” ወደማለት ሊሸጋገር ይችላል።

እንዲህ ዓይነቱ ስልቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ግን የመላው ሕዝብ ተሳትፎ እና የተቀናጀ አሠራርን ይፈልጋል። ለምሳሌ፣ ሰብስቡ ሲባል መሰብሰብን፤ በትኑ ሲባል መበተን ይጠይቃል። እንዲህ ዓይነት የተቀናጁ የጋራ እርምጃዎች በአምባገኑ የህወሓት አገዛዝ ላይ ከሚያደርሱት ጥቃት በተጨማሪ በኢትዮጵያዊያን መካከል ያለውን መግባባት ያጠናክራሉ። እንዲህ ዓይነት የተቀናጁ የጋራ እርምጃዎች በማኅበረሰብ ቡድኖች መካከል አዎንታዊ መስተጋብር ለመፍጠር የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው።
አሁን አገራችን የምትገኝበት ሁኔታ በጥሞና ሲጤን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይነጋገር መግባባት፣ እርስ በርሱ መናበብ የሚችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑ መረዳት ይቻላል። ይህ ስነልቦናዊ ዝግጅት ደረጃ በደረጃ ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያዘጋጀናል።
በማናቸውም የጋራ እርምጃዎች ለግል ጥቅሞቻቸው ቅድሚያ የሚሰጡ፤ ራሳቸው “ብልጥ” አድርገው በማየት በተፈጠረው ሁኔታ መጠቀም የሚፈልጉ፤ በሌላው ድካም ለማትረፍ የሚሯሯጡ ሰዎች መኖራቸው የማይቀር ነው። ህወሓት ለሃያ አራት ዓመታት ኮትኩቶ ያሳደገው የአድርባይነት ባህልም ሌላው እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል መገመት ቀላል ነው። ድህነት ደግሞ በገዢዎች ላይ ጨክነን የመነሳት አቅማችንን እንደሚያዳክም የታወቀ ነው። ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፊቱ የቀረበለት ምርጫ “ባርነት ወይስ ነፃነት” መሆኑን የተገነዘበበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

በዚህም ምክንያት ለህወሓት ባርነት ከመገዛት ነፃነትን የሚመርጥ ዜጋ ሁሉ ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀት ይኖርበታል። ለሁላችንም የሚሆን የትግል ዘርፍ መኖሩ የሕዝቡን ተሳትፎ ከፍ ያደርገዋል። የሁለገብ ትግል ስትራቴጂ ጥቅሙም እዚህ ላይ ነው። ማንም የማንም ነፃ አውጭ አይደለም። ሁላችንም ተባብረን ሁላችንንም ነፃ እናወጣለን።

አርበኖች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ትግላችን ዘርፈ ብዙ ነው፤ ተግባራዊ ትግል የሚደረገውን በሁሉም ቦታዎች ነው፤ እርጃዎቻችን እናቀናጅ፤ ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው” ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

   facebook
   google_buzz
   twitter
   rss
   print
   bookmark
   email


Breaking News: 4 Ethiopian Air force members defected (ESAT)
  
 Ethiopian Air Force members defection is continue, the latest defect was 4 Air Force members based in Dire Dewa Air force base. According to ESAT News the 4 Ethiopian Air force members are defected to Kenya.


Ginbot 7 Force leaders Zemene Kasse and Girmachew address Ginbot 7 town hall meeting in Switzerland

Ginbot7 force Right now Democratic fighter Zemene Kasse is speaking via Skype from Eritrea . He said “I am fine as you case see me” . He will be followed by  democratic fighter Girmachew, who abandon life in lucerne Switzerland to join the struggle for democracy in Ethiopia.
The meeting in Switzerland is now being attended by several Ethiopians. The attendants are emotionally following. Ginbot7 would like to clarify in the strongest possible terms that the struggle for freedom and democracy in Ethiopia will indeed continue without any hindrance and Ethiopia will surely prevail. The invited guests of honor heroes Zemene and Getachew are now speaking via Skype from the vicinity of battle field. Abbay Media will continue to update you live and will bring all the details as the news unfolds.
more


        ካለፈው ዓመት ተምረን በአዲስ ዓመት ደግሞ ይሄን አደርጋለሁ እንዲህ እሆናለሁ በዚህ እሄዳለሁ ብለን ዕቅድ አውጥተን በአዲስ ዓመትን ተሰፋ አድርገን ለመሽጋገር እንሞክራለን :: ባለፉት ዓመታት አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከብርሃን ወደ ጭለማ፣ ከዕድገት ወደ ድህነት፣ በሃገር ላይ ከመበልፀግ ወደ ሰደት ፣ ዕስር እና ሞት የተፈራረቁበት ነው :: አዲስ ዓመት መጣ እንክዋን አደረሳችሁ እየተባባልን ነው እናማ ይህን ሰስማ እነዚህ ከልጆቻቸው ከባለቤታቸው እና ከወዳጆቻቸው ተመንጭቀው በአንባገነኑ ወያኔ ቃልቲና ማእከላዊ የታሰሩት ወገኖቼ እና ቤተሰቦቻቸው ትዝ አሉኝ :: ለመሆኑ ለነሱ ይህ አዲስ ዓመት ምን ማለት ይሆን ? ለመላው ኢትዮጵያስ ?
የወያኔው መንግስት የ40 ዓመት ዕቅድ አለኝ እያለ ያንን ደግሞ ማንም እንዲያሰናክለው እንደማይፈቅድ እና ዕቅዱን ሊያስናክሉብኝ ይችላሉ ያለውን በማሰር እና ከሃገር እንዲሰደዱ በማድረግ ተያይዞታል:: እነሱ ኢትዮጵያን እና ሕዝቡን ለማጥፋት የ40 ዓመት ዕቅድ ሊያሳኩ ቀን ከለሊት ሲጥሩ እኛ ኢትዮጵያን እና እራሳችንን ለማዳን ቀን ከለሊት መሰራት እንዴት ያቅተናል ? የመጪው ዓመት የሰላም እና የፍትህ እንዲሆን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን አስከፊ አገዛዝ ይበቃሃል ሊለው ይገባል :: አንድነት ሃይል ነው እና አኔ አንተ ማለት ትተን " እኛ " በማለት እጅ ለእጅ ተያይዘን ከዚህ ሰርዓት እራሳችንን ነፃ ማውጣት ይጠበቅብናል :: ሰለዚህ የመጪው ዓመት የለውጥ እንዲሆንልን እመኛለሁ :: እነዚህ ወገኖቼም በሃገራቸው ኢትዮጵያ ፍትህ እኩልነት እንዲሰፍንባት መሰዋዕትነት እየከፈሉ ሲሆን ለዛ ደግሞ የመጪው ዓመት ሃገራቸው ኢትዮጵያ ነፃ ወታ እነሱም ለቤታቸው እና ለቤተሰቦቻቸው እንዲበቁ እመኛለሁ :: ኑ እጅ ለ እጅ ተያይዘን ሃገራችንን ኢትዮጵያን የባርነት ቀንበር አንስተን ፍትህ እኩልነት እና ነፃነት የተሞላች ኢትዮጵያን እንገንባ !!!
2007 የነፃነት ጮራ ይፈንጥቅበት !!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

Human Rights Watch – Fears for Safety of Returned Opposition Leader
July 8, 2014 | Filed underEnglish,Human Rights


         
(London) – An exiled Ethiopian opposition leader unlawfully deported by Yemen back to Ethiopia is at risk of mistreatment including torture. Andargachew Tsige is secretary-general of Ginbot 7, a banned Ethiopian opposition organization, and was convicted and sentenced to death in absentia in separate trials in Ethiopia in 2009 and 2012.
The current whereabouts of Andargachew, a British national, is unknown, raising concerns for his safety. The Ethiopian government should take all necessary steps to ensure Andargachew’s safety and his right to a fair trial. Many individuals arrested in politically related cases in Ethiopia are detained in Addis Ababa’s Maekelawi prison. In an October 2013 report, Human Rights Watch documented the use of torture by authorities against detainees in Maekelawi, including members of opposition political parties and organizations, as well as journalists.
        
We are deeply concerned for Andargachew Tsige’s safety,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director. “Ethiopia needs to demonstrate that it is holding Andargachew in accordance with its international obligations, and he should be allowed immediate access to a lawyer, his family, and to British consular officials.  Leslie Lefkow, deputy Africa director
Yemeni officials arrested Andargachew at El Rahaba Airport in Sanaa, Yemen, on June 23 or 24, 2014, while he was in transit on a flight from Dubai to Eritrea. They did not permit him consular access to UK embassy officials and summarily deported him to Ethiopia, credible sources told Human Rights Watch, despite his being at risk of mistreatment.
Yemeni authorities initially denied any knowledge of Andargachew’s detention and transfer to Ethiopia. Ethiopian government officials publicly called for his extradition from Yemen on July 3.
      
Under the Convention against Torture, which Yemen ratified in 1991, a government may not “expel, return (‘refouler’) or extradite a person to another State where there are substantial grounds for believing that he would be in danger of being subjected to torture.” These protections override any extradition treaty or other security arrangement that may exist between Yemen and Ethiopia.
Trials in absentia generally violate the defendant’s right to present an adequate defense, concerns heightened in cases involving the death penalty.
“Yemen blatantly violated its international legal obligations by deporting someone to Ethiopia who not only is at serious risk of torture, but also faces the death sentence after being tried in absentia,” Lefkow said.
Ginbot 7, of which Andargachew is a founding member, was established in the aftermath of Ethiopia’s controversial May 2005 national elections. The Ethiopian government banned Ginbot 7, which has advocated the armed overthrow of the Ethiopian government, and officially considers it to be a terrorist organization.
The government has prosecuted Ginbot 7 members and leaders in trials that did not meet international fair trial standards. In November 2009, a court convicted Andargachew and 39 others under the criminal code on terrorism-related charges. Andargachew, who was tried in absentia, was sentenced to death. In June 2012, he was convicted again in absentia, this time under the abusive 2009 anti-terrorism law, along with 23 journalists, activists, and opposition members. Again, he was sentenced to death.
Human Rights Watch has repeatedly criticized provisions in Ethiopia’s anti-terrorism law that violate due process rights guaranteed under Ethiopian and international law. At least 34 people, including 11 journalists and four Ginbot 7 leaders, are known to have been sentenced under the law since late 2011 in what appeared to be politically motivated trials; the real number is likely much higher. Suspects held under the law may be detained for up to four months without charge, among the longest periods under anti-terrorism legislation worldwide.
      
Ethiopian courts have shown little independence from the government in politically sensitive cases. Defendants have regularly been denied access to legal counsel during pretrial detention, and complaints from defendants of mistreatment and torture have not been appropriately investigated or addressed – even when defendants have complained in court.
The Ethiopian government routinely denies that torture and mistreatment occurs in detention. It restricts access to prisons for international observers, monitors, and consular officials, making it difficult to monitor the number and treatment of prisoners. In several cases documented by Human Rights Watch, Ethiopian security officials have arrested foreign nationals, denied knowledge of their whereabouts, and delayed access for consular officials for long periods.
       
In 2007 Human Rights Watch documented the forced transfer of scores of men, women, and children from Somalia and Kenya to Ethiopia. One of the men, Bashir Makhtal, a Canadian citizen of Ethiopian origin who was accused of membership of the Ogaden National Liberation Front (ONLF), a banned armed movement in Ethiopia, was denied consular access for 18 months. Meanwhile in 2010 and again in 2012, refugees registered with the United Nations High Commissioner for Refugees in Kenya were unlawfully returned to Ethiopia and told Human Rights Watch that they were subsequently tortured in detention. In all of these cases, the individuals were accused of belonging to groups that the Ethiopian government has designated as terrorist groups.
  
“Given its appalling track record of mistreating members and perceived supporters of banned groups, Ethiopia should know that the world will be watching how it treats Andargachew Tsige,” Lefkow said.
Source: http://www.hrw.org/


Free Andargachew tseges demo in Germany


“አገራችንን በእርቅ እንታደጋት” ዶ/ር ተጋ
"ዋስትና የናፈቃቸው ባለስልጣናት አሉ" 
 
 
 
 
 
ethiotoday.eu
Back to content | Back to main menu